HIVN tube

17ሺ ሰብስክራይብ 🙏 አመሰግናለሁ 🙏

5 days ago | [YT] | 6

HIVN tube

እንኳን ለ2017 ዓም ዘመነ ማቴዎስ በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን ::

በአዲሱ ዓመት መጥፎውን ሁሉ አርቆ መልካሙን የምናይበትና እቅዳችን የምናሳካበት ያድርግልን::

1 week ago | [YT] | 10

HIVN tube

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ | የፈተና ማብራሪያ
____

ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Public Health, Pharmacy, Anesthesia, Medical Laboratory Science, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing እና Surgical Nursing ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ፤ ፈተናው ከመስከረም 8 - 10/ 2017 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ መሆኑን እየገለፅን፦

1. የፈተናው መርሃ-ግብር
- 8/1/2017 ዓ.ም…… Medicine, Pharmacy, Anesthesia, Dental Medicine, Environmental Health, Psychiatric Nursing and Surgical Nursing
- 9/1/2017 ዓ.ም……… Medical Laboratory Science, Midwifery, Pediatric and Child Health Nursing, Medical Radiology Technology and Public Health
- 10/1/2017 ዓ.ም…………… Nursing
እያንዳንዱ ተፈታኝ ከሚፈተንበት ቀን አንድ ቀን ቀደም ብሎ ማለትም መስከረም 7/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ 3፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (orientation) መከታተል፤ የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራትና፤ የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል::

2. በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡

3. ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡

4. በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት በኋላ) አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረማችሁን ማረጋገጥ ይኖርባችኋዋል፣

5. ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን QR code ያለው የፈተና መግቢያ /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

▫ የመፈተኛ ጣቢያ ኦንላይን በመረጣችሁት መሰረት ስም ዝርዝራችሁን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ /Link/ በመጫን መመልከት ይኖርባችኋል፡፡ (drive.google.com/drive/folders/17QzuVtjm4Uh3yQhA-t…)
▫ ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት ተቋም ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ የማትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፦
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ(ቴዎድሮስ ካምፓስ) የመፈተኛ ጣቢያ የመረጣችሁ ተመዛኞች ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ(ጤና ሳይንስ ኮሌጂ) የተዘዋወራችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

✔ወቅታዊ የስራ ቅጥር መረጃዎችን በየጊዜው ለማግኘት ቻናላችንን ይከታተሉ::
🩵 t.me/addlist/IWOV6uABAi5lYTA0 
🖥 youtube.com/@HIVN
📱 fb.com/healthinovation/

1 week ago | [YT] | 4

HIVN tube

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ፈተናውን ማለፍ የቻሉት 5 ነጥብ 4 በመቶ ብቻ ናቸው - የትምህርት ሚኒስቴር

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 36 ሺህ 409 ፈተናውን አልፈዋል

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 674 ሺህ 823 ተማሪዎች መካከል ማለፊያ ነጥብ ያስመዘገቡት 36 ሺህ 409 ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል ማለፍ የቻሉት 5 ነጥብ 4 በመቶ ብቻ ናቸው ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክተው ዛሬ ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ.ም መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በሀገር አቀፍ ደረጃ 1 ሺህ 363 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ገልጸዋል።

የዘንድሮው ዓመት አጠቃላይ ውጤት ካለፉት ሁለት ዓመታት አንጻር የተሻለ መሆኑንም ተናግረዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል ከ600 ከታረመው ፈተና ከፍተኛው ውጤት 575 መሆኑን ተናግረዋል። ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 1 ሺህ 220 የሚሆኑት ከ500 በላይ ውጤት ማምጣታቸውን ገልጸዋል።

ከነዚህም መካከል 384 ቱ ሴቶች መሆናቸውን አስታውቀዋል። ተፈታኝ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ መግለጻቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

       @healthinovation

1 week ago | [YT] | 2

HIVN tube

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ፡፡


(ጷጉሜ 4/2016 ዓ.ም) የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡


ተማሪዎቹ ውጤታቸውን ከሌሊቱ 6 ሠዓት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡


የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በሰጡት መግለጫ÷ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡ 701 ሺህ 749 ተማሪዎች መካከል 684 ሺህ 205 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል ብለዋል ።


ቀሪዎቹ በተለያዩ ምክንያቶችና ትምህርታቸውን ዘግይተው በመጀመራቸው ፈተናውን አለመውሰዳቸውን ገልጸዋል ።


ከተፈታኞቹ ውስጥ 29 ሺህ 736 ያህሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የኦንላይን ፈተና አማካኝነት ፈተናቸውን ወስደዋል ነው ያሉት፡፡


ዘንድሮ ፈተና ከወሰዱት አጠቃላይ ተማሪዎች ያለፉት 5 ነጥብ 4 በመቶ መሆናቸውን ጠቅሰው÷ አዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር እንዲሁም ሐረሪ እና ኦሮሚያ ክልሎች ከአስፈተኗቸው ውስጥ የተሻለ ቁጥር ማሳለፋቸውን ገልጸዋል፡፡


ሁሉም ክልሎች በአለፈው ዓመት ከአስፈተኗቸው ተማሪዎች ቁጥር አንጻር ዘንድሮ የተሻለ ማሳለፍ መቻላቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

@healthinovation

1 week ago | [YT] | 4

HIVN tube

የ12ኛ ክፍል ውጤትዎን ይመልከቱ!

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ለሊት 6:00 ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ መገለፁ ይታወቃል።

በሚከተሉት አማራጮች ውጤታችሁን ተመልከቱ፦

► በፖርታል 👉 result.eaes.et/

► በአጭር የፅሑፍ መልዕክት 👉 6284

► በቴሌግራም ቦት 👉 t.me/EAESbot

ከውጤት መግለጫ ፖርታል እና ቴሌግራም ቦት ላይ ጊዜያዊ ሰርቲፊኬት ማውረድና ማተም እንደምትችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ተፈታኞች በውጤት እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ቅሬታ ካላቸው ወደ አገልግሎቱ ቢሮ በአካል መሔድ ሳያስፈልጋችሁ ከSMS በስተቀር በውጤት መግለጫ አማራጮቹ ላይ Compliant የሚለውን በመጫን የቅሬታቸውን ዓይነት በተዘጋጀ የቅሬታ ፎርም ላይ በትክክል በመሙላት ማቅረብ ትችላላችሁ።

አገልግሎቱ በቅሬታችሁ ላይ ምላሽ ቅሬታቸውን ባቀረቡበት ተመሳሳይ አድራሻ የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጿል።

1 week ago | [YT] | 4

HIVN tube

#አኃዛዊ_መረጃ

674,823
በ2016 ዓ.ም ለ12ኛ ክፍል ፈተና የተቀመጡ

36,409 (5.4%)
ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች

1,363
አንድም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች

9%
ፈተናውን ከወሰዱ 321,536 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ውስጥ ማለፍ የቻሉት

2%
ፈተናውን ከወሰዱ 353,287 የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ውስጥ ማለፍ የቻሉት

26.6%
በኦንላይን ለፈተናው ከተቀመጡ ማለፍ የቻሉ

29.76%
ዘንድሮ የተመዘገበው አማካይ ውጤት (Mean)

575 (ከ600)
በተፈጥሮ ሳይንስ የተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት (በአዲስ አበባ ካቴድራል ት/ቤት)

538 (ከ600)
በማኅበራዊ ሳይንስ የተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት (በአዲስ አበባ ኢትዮ ፓረንትስ ት/ቤት)

675 (ከ700)
በትግራይ ክልል የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት
(ከቓላሚኖ ልዩ ትምህርት ቤት)

2 ትምህርት ቤቶች
ሙሉ በሙሉ ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ያሳለፉ
(እቴጌ መነን የሴት ተማሪዎች አዳሪ ት/ቤት እና ገላን የወንድ ተማሪዎች አዳሪ ት/ቤት)

1 week ago | [YT] | 3

HIVN tube

የመንግስት ሠራተኞች ጥናቱ በሚኒስትሮች ምክር:- ቤት ቀርቦ ከመፅደቁ በፊት

አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ እንደጠበቅነዉ አይደለም ያሉ የተለያዩ የመንግስት ስራተኞች ጥናቱ በሚኒስትሮች ምክር-ቤት ቀርቦ ከመፅደቁ በፊት በድጋሚ መታየት እንዳለበት መናገራቸውን ካፒታል ዘግቧል።

ከመስከረም 1 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው አዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ ጥናት የሚኒስትሮች ምክር-ቤት ከማፅደቁ አስቀድሞ ሰራተኞችን ማወያየት እንዳለበት እና በድጋሚ መታየት እንደሚኖርበት ተጠይቋል ያለው ካፒታል ያነጋገራቸው ሠራተኞች እንደገለፁት የደመወዝ ማሻሻያው አሁን ያሉበትን የኑሮ ሁኔታ እንደተባለውም ከግምት ያላስገባና እንደጠበቁት እንዳልሆነ አስረድተዋል።

''ስለደመወዝ ማሻሻያው ጠ/ሚኒስትሩ በተናገሩበት ሰዓት እጅግ በጣም ጠብቄ ነበር ነገር ግን አሁን ከዛ የተለየ ነገር ነው የሆነው'' ሲሉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አዲስ አበባ ውስጥ በአንድ የመንግስት ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ መምህር ነግረውኛል ብሏል።

የደመወዝ ማሻሻያ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ ከመኖሪያ ቤት ኪራይ ጀምሮ ከምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎችን ጨምሮ የዋጋው ንረቱ በእጥፍ እንደጨመረ ሠራተኞቹ ለካፒታል ያቀረቡት ቅሬታ ያመላክታል።

ይህ እንኳን ተፈፃሚ ይሁን ከተባለ የስራ ግብር እንዲቀነስ መደረግ አለበት በማለት ተናግረዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደመወዝ ጭማሪን በሚመለከት ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከፌደራል መንግስት ባለስልጣናት እና ከግል ባንኮች ፕሬዝዳንቶች ጋር በተደረገ ውይይት ላይ እንደተናገሩት " በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የመንግስት ሰራተኞች የሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ “በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም” ብለዋል።

በአዲሱ እርከን ከተካተቱት የመንግስት ሰራተኞች ዉስጥ የጤና ባለሞያዎች ይገኙበታል። ካፒታል ያነጋገራቸዉ እነዚህ ባለሞያዎች እንደሚሉት " ቀድሞ የመሰለን ጭማሪዉ በአንድ ጊዜ እስከ 10 ሺህ ብር የሚያህል ገንዘብ ቢሆንም በተቃራኒው የሆነዉ ግን ያሳዝናል ። አሁን ላይ ከ 1500 ብር በታች ነዉ የተጨመረዉ ይህ ደግሞ ተመልሶ በስራ ግብር የሚቀነስ መሆኑ የተደረገዉ ጭማሪ ሳይሆን ተስፋ ብቻ ነዉ በማለት ቅሬታዎች አቅርበዋል።

የደሞዝ ጭማሪ መኖሩን መንግስት መናገሩን ተከትሎ በማግስቱ  የሁሉም ነገር ዋጋ በሁለት እጥፍ ጨምሯል። በዚህም ሰራተኛዉም ሆነ በዝቅተኛ ኑሮ ላይ የነበሩት ሰዎች ምንም የተሰጣቸዉ ነገር ሳይኖርና ጭማሪ እጃቸዉ ሳይገባ የኑሮ ዉድነቱ ተባብሶ ቀጥሏል ሲሉም ሁኔታዉን በምሬት ገልፀዉታል።

ከቀናት በኃላ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀዉ ረቂቅ ጥናቱ ላይ እንደተገለፀዉ ዝቅተኛው ደረጃ የመነሻ ደመወዝ በመንግስት መሥሪያ ቤቶች አሁን በሥራ ላይ ካለው ብር 1,100 የመነሻ ወደ 4760 ወይም 332.73% የተደረገ ሲሆን ፤

ከፍተኛው ደረጃ የመነሻ ደመወዝ ደግሞ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ የፕሮፌሰር የሥራ መደብ ካረፈበት የመነሻ ደመወዝ ብር 20,468 ሲሆን ይህ ተደርጎል የተባለዉ ጭማሪ በ5% በመቶ ወይም 1023 ብር እንደሆነ ካፒታል በረቂቅ አዋጁ ተመልክቷል ።

ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ለዉሳኔ የቀረበዉ እና በገንዘብ ሚኒስትር እንዲሁም በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አማካኝነት ጥናት ተደርጎበታል የተባለው ይህ የሠራተኞች የኑሮ ውድነት ጫና መደጎሚያ ደመወዝ ማሻሻያ ረቂቅ ለሚኒስትሮች ምክርቤት በቀን 28 /12/ 2016 ዓ.ም. ነዉ መቅረብ ለማወቅ የተቻለው።
#ካፒታል

✔ወቅታዊ የስራ ቅጥር መረጃዎችን በየጊዜው ለማግኘት ቻናላችንን ይከታተሉ::
🩵 t.me/addlist/IWOV6uABAi5lYTA0 
🖥 youtube.com/@HIVN
📱 fb.com/healthinovation/

📱🖥📱🌐📱📱📱

1 week ago | [YT] | 14

HIVN tube

16K followers 🙏 Thank you for your support
‪@HIVN‬ #ethiopia

1 week ago | [YT] | 3

HIVN tube

15K subscribers 🙏
#ethiopia ‪@HIVN‬

2 weeks ago | [YT] | 3