HIVN tube

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ፡፡


(ጷጉሜ 4/2016 ዓ.ም) የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡


ተማሪዎቹ ውጤታቸውን ከሌሊቱ 6 ሠዓት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡


የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በሰጡት መግለጫ÷ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡ 701 ሺህ 749 ተማሪዎች መካከል 684 ሺህ 205 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል ብለዋል ።


ቀሪዎቹ በተለያዩ ምክንያቶችና ትምህርታቸውን ዘግይተው በመጀመራቸው ፈተናውን አለመውሰዳቸውን ገልጸዋል ።


ከተፈታኞቹ ውስጥ 29 ሺህ 736 ያህሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የኦንላይን ፈተና አማካኝነት ፈተናቸውን ወስደዋል ነው ያሉት፡፡


ዘንድሮ ፈተና ከወሰዱት አጠቃላይ ተማሪዎች ያለፉት 5 ነጥብ 4 በመቶ መሆናቸውን ጠቅሰው÷ አዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር እንዲሁም ሐረሪ እና ኦሮሚያ ክልሎች ከአስፈተኗቸው ውስጥ የተሻለ ቁጥር ማሳለፋቸውን ገልጸዋል፡፡


ሁሉም ክልሎች በአለፈው ዓመት ከአስፈተኗቸው ተማሪዎች ቁጥር አንጻር ዘንድሮ የተሻለ ማሳለፍ መቻላቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

@healthinovation

1 week ago | [YT] | 4